አዲስ አበባ | ህዳር 26፤ 2016| NBC ETHIOPIA- የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ኢትዮጵያ የዓለም ሥራ ድርጅት(ኣይ.ኤል.ኦ) አባል የሆነችበት 100ኛ ዓመትን እየተከበረ ነው። ሀገሪቱ በድርጅቱ አባል ከሆነችበት ወቅት አንስቶ የተለያዩ የአሰሪ እና ሰራተኛ ህጎችን እና መመሪያዎችን ተግባራዊ ስታደርግ መቆየቷን በክብረ በዓሉ ላይ ተመላክቷል።

“ማህበራዊ ምክክርና የላቀ ምርታማነት ለማህበራዊ ፍትህ” በሚል መሪ ሀሳብ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ብሄራዊ የአሰሪ እና ሰራተኛ ጉባኤ ማጠናቀቂያ መርሀ ግብር ተካሂዷል።
በዕለቱም ምቹ የስራ ሁኔታ መፍጠር፣ የአሰሪ እና ሰራተኛ ግንኙነትን ማጠናከር የስደተኛ ሰራተኞች መብት ማስከበር እንዲሁም ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ሁኔታ እንዲፈጠር በማድረግ በግብርና፣ ኢንዲስትሪ እና አገልገሎት ዘርፍ ላይ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የመንግስት እና የግል የልማት ድርጅቶች እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በሀገሪቱ የሚገኙ ዘጠኝ የሰራተኛ ፌዴሬሽኖች ለሰራተኞች የተመቻቸ የስራ አከባቢ በመፍጠር እና የሰራተኞችን መብት በማክበር እና በማስከበር ላበረከቱት ሚና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በሀሴት ሀይሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












