አዲስ አበባ | ህዳር 25፤ 2016| NBC ETHIOPIA–የአዲስ አበባ መንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን የብሉምበርግ ኢኒሼዬቲቭ ፎር ግሎባል ሮድ ሴፍቲ አጋር ድርጅት ከሆነው ቫይታል ስትራቴጂስ ጋር በመተባበር በፍጥነት ማሽከርከር ላይ ያተኮረ እና ‘’ፍጥነት ይገድላል፤ በዝግታ ያሽከርክሩ!’’ በሚል መሪ ቃል ከተማ አቀፍ የብዙኃን መገናኛ ንቅናቄ በይፋ አስጀምራል።
የብዙኃን መገናኛ ንቅናቄ ለ4 ሳምንታት የሚቆይ ሲሆን በፍጥነት ማሽከርከር ላይ ያተኮሩ መልዕክቶች በማኅበራዊ ሚዲያዎች፣ በህትመት ውጤቶች እና በሌሎች የመልዕክት ማስተላለፊያ ዘዴዎች አማካኝነት እንዲተላለፉ ይደረጋል ተብሏል ።
የአዲስ አበባ መንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ዋና ዳይሬክተር ክበበው ሚደቅሳ በአዲስ አበባ ከሚከሰቱ የትራፊክ አደጋዎች ዋነኛው መንስኤ በፍጥነት ማሽከርከር ነው ያሉ ሲሆን የንቅናቄው አላማም በፍጥነት በማሽከርከር የሚከሰተውን የሞትና የአካል ጉዳት መቀነስ እንዲቻል የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ የባህሪ ለውጥ እንዲያመጣ ማድረግ ነው ብለዋል።
የአዲስ አበባ መንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን በከተማዋ እየተከሰተ ያለውን የመንገድ ትራፊክ አደጋ ለመቀነስ በርካታ ሥራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ በመድረኩ ተገልጿል።
በሰላማዊት ወልደገሪማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#ሆኖ_መገኘት












