አዲስ አበባ | ህዳር 20፤ 2016| NBC ETHIOPIA – ጁንግ ዮ-ጁንግ የተባለችው የ23 ዓመት ወጣት ደቡብ ኮርያዊት ወጣት ሰውን መግደል የሚፈጥረውን ስሜት ለማወቅ ካላት ጥልቅ ፍላጎት የተነሳ የማታውቀውን ሰው የገደለች ሲሆን በዕድሜ ልክ እስራት ተቀጥታለች።
ፖሊስ ወጣቷ ሰውን ለመግደል ሙከራ ለማድረግ አስባ የማታውቃትን የእንግሊዘኛ ቋንቋ መምህርት በስለት ደጋግማ ወግታ ገድላለች ብሏል።
ዐቃቤ ሕግ የወንጀሉን ድርጊት ለፍርድ ቤት ሲያስረዳ፤ ሥራ አጥ እና ብቸኛ የሆነችው ጁንግ የምትገድለውን ሰው ለመለየት ለወራት ያክል ስታስስ ቆይታለች።
ለዚህም ወጣቷ የቋንቋ መማሪያ መተግበሪያን በመጠቀም እንግሊዘኛ ቋንቋ በቤታቸው ያስተምሩ እንደሆነ ከ50 በላይ ሰዎችን ለማነጋገር ሞክራለች።
ግንቦት ወር ላይ እንግሊዘኛ ቋንቋ መማር የምትፈልግ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እና እናት መስላ አንዲት ሴት መምህርትን ማነጋገር ጀምራለች።

ጁንግ ወንጀሉን የፈጸመችው በደቡብ ምሥራቅ ደቡብ ኮሪያ ውስጥ ቡሳን ከተማ ነዋሪ ወደሆነች እና በስም ወዳልተጠቀሰች የ26 ዓመት ሴት መምህርት ቤት ካመራች በኋላ ነው።
ጁንግ ከኢንተርኔት ላይ የገዛችውን የትምህርት ቤት የደንብ ልብስ ለብሳ ከመምህሯ ቤት ተገኝታለች።
መምህርቷ ወደ ቤቷ ዘልቃ እንድትገባ ከፈቀደች በኋላ ከ100 ጊዜ በላይ በስለት ወግታ እንደገደለቻት ዐቃቤ ሕግ አመልክቷል።
ወንጀለኛዋ ጁንግ የተጎጂዋ ሕይወት ካለፈ በኋላ እንኳ የመምህርቷን አካል በስለት መውጋት ቀጥላላለች ሲል ፖሊስ አስታውቋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












