አዲስ አበባ | ህዳር 18፤ 2016| NBC ETHIOPIA- የገቢዎች ሚኒስትር ባለፉት 4 ወራት ገቢውን ለማሻሻል ከተለያዩ ሚኒሰትር መስሪያ ቤቶች ጋር በጋራ ሲሰራ እንደነበር እና የተሸለ ገቢ ማስመዝገቡን ገልጿል፡፡

በበጀት አመቱ በ4 ወራት ውስጥ 196.3 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 193.9 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 98.78 በመቶ ማሳካቱን የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ አስታውቀዋል፡፡
ሚኒስትሯ ከሀገር ውስጥ ገቢ 128.49 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 129.18 ቢሊየን መሰብሰብ እንደቻለ እና ከዚህ በተጨማሪም ከውጭ ንግድ ቀረጥ እና ታክስ 67.88 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 64.79 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡
እንደ ሀገር ከሰላም እጦት ጋር በተያያዘ ትልቅ ተግዳሮት ቢኖርም እሱን በመቋቋም የተሸለ ገቢ ማስገባታቸውን ሚኒስትሯ ገልጸዋል፤ በተለይም በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ባለው የሰላም እጦት በባህርዳር እና በኮምቦልቻ ችግር ያጋጥመናል ብለን ሰግተን የነበረ ቢሆንም ያሳይሆን በመቅረት በኮምቦልቻ የሚገኘው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቢሮ 99 በመቶ እቅዱን ማሳካቱን ሚኒስትሯ በሰጡት መግለጫ ጠቅሰዋል፡፡
በኮንትሮባድ ከተጠረጠሩ 312 ሰዎች ውስጥ 258 የሚሆኑትን በቁጥጥር ስር በማዋል አስተማሪ እርምጃ መውስዱ ተገልጿል፡፡
በየአብስራ ሚሊዩን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












