አዲስ አበባ | ህዳር 17፤ 2016| NBC ETHIOPIA – የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከጤና ሚኒስትር፤ ከክልል ጤና ቢሮዎች እንዲሁም ከአጋሮች ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

ስምምነቱም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ዜጎች የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን ኢንዱስትሪ ፓርኮችም በተመጣጣኝ ዋጋ ለሰራተኞች የጤና አገልግሎት ማቅረብ እንዲችሉ ያግዛል ተብሏል።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በስምምነት መድረኩ ላይ የሰነዶቹ መፈረም የኢትዮጵያ መንግስት ለቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየበት መሆኑን ያስገነዘቡ ሲሆን የስራው ባለቤት በዋናነት ክልሎች በመሆናቸው ትኩረት ሰጥተው በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከ80 ሺህ በላይ ወጣቶች የስራ እድል ማግኘት መቻላቸውን ፤ እነዚህ ወጣቶች ተገቢውን የስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት እንዲያገኙ ከጤና ሚኒስቴር እና የክልል ጤና ቢሮዎች ጋር ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽንና ማኔጅመንት ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሚል ኢብራሂም ገልጸዋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












