አዲስ አበባ | ህዳር 14፤ 2016| NBC ETHIOPIA- የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ልዩ ትኩረት ከትሰጣቸው ዘርፎች መካከል የማእድን ዘርፍ አንዱ መሆኑን በ2ኛው አመታዊ የማዕድንና ቴክኖሎጂ (MINTEX) ኤክስፖ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ተናግረዋል::

በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) በበኩላቸው ባለፉት ሶስት አመታት የተፈጠረው አለመረጋጋት ዘርፉ በታሰበው ልክ እንዳያድግ እንቅፋት መሆኑን አስረድተዋል::
በኤክስፖው ላይ በዘርፉ የተሰማሩ ከ90 በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ድርጅቶች ምርቶቻቸውን ለጎብኚዎች አቅርበዋል::
በአክረም ኑርያ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












