አዲስ አበባ | ህዳር 14፤ 2016| NBC ETHIOPIA- የደቡብ አፍሪካ ምክር ቤት የተቃዋሚውን መሪ ጁሊየስ ማሌማን ለምጣኔ ኃብት እኩልነት የሚታገለው ፓርቲው ‘ኢኮኖሚክ ፍሪደም ፋይተርስ’ አምስት አባላትም እንዲሁ እግድ ተጥሎባቸዋል።

የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ በኬፕታውን አዳራሽ ብሄራዊ ንግግር እያደረጉ በነበረበት ወቅት ጁሊየስ ማሌማ እና ሌሎች አባላቱ መድረኩን በመረበሻቸው ፓርላማውን ንቀዋል ተብሏል።
ፓርላውንም በመናቅ ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል የተባሉት የምክር ቤቱ አባላት በታገዱበት በአንድ ወር ወቅት ያለውንም ደመወዝ አይከፈላቸውም።
ማሌማ እና ሌሎች የምክር ቤቱ አባላት ከአዳራሹ በጸጥታ ኃይሎች እንዲወጡ የተደረጉ ሲሆን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤም ሂደቱ እንዲቋረጥ አድርገዋል፡፡

የእግዱን ውሳኔ ያስተላለፈው የፓርላማው ኮሚቴ እንዳስታወቀው የፕሬዚዳንቱን መግለጫ አቋርጠው በመበጥበጣቸው እና የሀገሪቱንም ምስል በማጠልሸታቸው እነዚህ የምክር ቤቱ አባላት በአካል ፕሬዚዳንቱን ፤ አፈ ጉባኤውን እና ህዝቡንም ይቅርታ እንዲጠይቁ ተወስኖባቸዋል።
ስድስቱ የምክር ቤት አባላት እግድ የሚጀምረው በመጪው ጥር ወር ሲሆን ፕሬዚዳንቱ በየካቲት ወር ሊያደርጉት ያቀዱት ብሄራዊ ንግግር እንደሚያመልጣቸው ቢቢሲ ዘግቧል
የምክር ቤቱ አባላቱ እግዱ እንዲተላለፍ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ መደረጉንም ተከትሎ ፓርላማው በነሱ ላይ በሚያሳልፈው ውሳኔ አልተገኙም።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት