አዲስ አበባ | ህዳር 13፤ 2016| NBC ETHIOPIA- የኢትዮጵያ የህፃናት መፅሀፍት እድገትና ተግዳሮት በሚል ርዕስ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የተዘጋጀ የሂስ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በመድረኩ የመነሻ ጥናታዊ ፁሁፍ የቀረበ ሲሆን በህፃናት ስነፅሁፍ ዘርፍ የሚነሱ ተግዳሮቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ተነስተዋል። በተለይም ለህፃናቶች የሚቀርቡ ፁሁፎች ምን ያክል የታነፁ ናቸዉ? ፁሁፉስ ይመጥናል ወይ የሚሉ ሀሳቦች ላይ ዉይይት ተደርጓል።
በሂስ መድረኩ ላይ ከተለያዩ ተቋማት የመጡ ግለሰቦች በልጆች መፅሃፍት ላይ የሚታዩ ክፍተቶችንና መስተካከል ያሉባቸዉን ጉዳዮችን አንስተዋል።
ለህፃናት ስነምግባርን ለማስተማርና እዉቀትን ለማስተላለፍ የስነፅሁፍ አስተዋፅኦ የጎላ በመሆኑ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የሁሉንም አካላት ተሳትፎ እንደሚፈልግ ተገልጿል።
ሊያ ክብሮም
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv