አዲስ አበባ | ህዳር 13፤ 2016| NBC ETHIOPIA- የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ አመት አፈፃፀም እየገመገመ ይገኛል። ቢሮው በበጀት አመቱ ለመሰብሰብ ያቀደውን ከ140ቢሊየን ብር በላይ ከግብ ለማድረስ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በስምምነት እየሰራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ አደም ኑሪ ገልፀዋል።

በግምገማው ቢሮው ከገቢዎች ሚኒስቴር፣ ጉሙሩክ ኮሚሽን፣ ከኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮ፣ ከባንኮች እና ትምህርት ቢሮዎች ጋር ከስምምነት በመድረስ በቅንጅት እየተሰራ ነው ተብሏል።
ስምምነቶቹ የታቀደውን ገቢ ከማሳካት ባለፈ ተግጋዮችን በተቀላጠፈ መንገድ ለማስተናገድ፣ አገልግሎት ከማዘመን፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ከማሳደግ አንፃር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው በግምገማ መድረኩ ተነስቷል።
በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ክፍያቸውን የሚፈፅሙ የደረጃ <ሐ> ከፋዮች ሙሉ በሙሉ የግብር ክፍያቸውን ቴክኖሎጂን በመጠቀም በቴሌ ብር እንከፍሉ መደረጉ ተገልጿል። በቀጣይም በደረጃ <ለ> እና <ሀ> ስር የሚገኙ ግብር ከፋዮችን ለማካተት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በሀሴት ሀይሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv











