አዲስ አበባ | ህዳር 11፤ 2016| NBC ETHIOPIA -የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2016 ዓ.ም አንደኛ ሩብ አመት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በትስስር የተከናወኑ ተግባራትና የተገኙ ውጤቶችን በመገምገም ላይ ይገኛል።

በበጀት አመቱ ቢሮው የከተማዋን ጸጥታ ለማረጋገጥ የተለያዩ ስራዎችን መስራቱን የቢሮው ሀላፊ ሊዲያ ግርማ ገልጸዋል።
በእዚህም መሰረት ህገወጥ ተግባራትን ከመከታተልና እርምጃ ከመውሰድ አንጻር መልካም ስራ መሰራቱ ተገልጿል።
ለእዚህም ከሀይማኖት ተቋማት፣ ሲቪክ ማህበራትና ሌሎች አካላት ጋር እየሰራ ይገኛል።
በእዚህም 8970 የጎዳና ተዳዳሪዎች ከጎዳና ተነስተው ወደማዕከላት እንዲገቡ መደረጉ በመድረኩ ተነግሯል።
ቢሮው ለደህንነት አስጊ ናቸው ያላቸው 1875 ጉዳዮች ላይ እርምት መወሰዱ ተገልጿል።
ባለፉት ሶስት ወራት 1791 በህገወጥ የመሬት ወረራ ሲካሄዱ የነበሩ ግንባታዎች ተገተዋል ተብሏል።

በተጨማሪም በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ1.8 ቢሊዮን በላይ ዶላር ተይዟል።
ከቁማረረ ቤቶቸረ ከአንድ ሚሊዪን ብር በላይ የተሰበሰበ ሲሆን አብዛኛው ከትምህርት ቤቶች አካባቢ እንደተሰበሰበ በመድረኩ ተገልጿል።
መድረኩ የከተማዋን ጸጥታ ማስጠበቅ ላይ የተሰማሩ አካላት በቀጣይ ሊሰሯቸው ለሚገቡ ስራዎች አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሏል።
በመድረኩ የቢሮውና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
መቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












