Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Health

የትልቁ አንጀት ካንሰር

November 20, 2023
in Health
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

 ????የትልቁ አንጀት ካንሰር የሚባለው

አዲስ አበባ | ህዳር 10፤ 2016| NBC ETHIOPIA -መነሻውን ከትልቁ የአንጀት ክፍል ያደረገ ማንኛውም ካንሰር የትልቁ አንጀት ካንሰር በመባል ይታወቃል። ትልቁ አንጀት በርዝመት መጠኑም ሆነ በስፋቱ ትልቅ የሚባል ሲሆን ሰገራ እስከሚወጣበት የታችኛው የአንጀት ክፍል ድረስ ይዘረጋል።

በተለምዶ የምግብ መብላላት ዑደት ከላይኛው የምግብ ቱቦ (Esophagus) ጀምሮ በጨጓራ እና በትንሹ አንጀት በኩል ካለፈ በኋላ ትልቁ አንጀት ላይ ይደርሳል። ይህ የተብላላው የምግብ ክፍል የመጨረሻውን መዳረሻ ፊንጢጣ ላይ በማድረግ ከሰውነት ይወገዳል። የካንሰር በሽታ ከእነዚህ ክፍሎች መነሻውን የማድረግ ዕድሉ ከፍተኛ ነው።

????ለትልቁ አንጀት ካንሰር አጋላጭ ምክንያቶች  ምንድናቸው?

-ዕድሜ ፦ በዕድሜ ጎልማሳ የሆኑ ግለሰቦች በዚህ በሽታ የመጠቃት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።

– አመጋገብ ፦  ለትልቁ አንጀት ካንሰር እንደዋነኛ አጋላጭ ምክንያትነት የሚታየው የተዛባ የአመጋገብ ስርአት ነው ።  በተለይ ቀይ ስጋን አዘውትሮ መመገብ ለምሳሌ ፦ የበሬ፣ የአሳማ እንዲሁም የበግ ቀይ ስጋን አዘውትረው የሚመገቡ ግለሰቦች፤ የታሸጉ እና በፋብሪካ የተቀመሙ የስጋ ተረፈ ምርቶችን አዘወትሮ መጠቀም፤ የስብ መጠኑ ከፍ ያለን ስጋ አዘወትሮ መመገብ (ጮማ ስጋ)፤ የፋይበር መጠኑ ያነሰ ምግብን አብዝቶ መመገብ እንዲሁም አልኮልን ከመጠን በላይ አዘውትሮ መጠቀም ለዚህ በሽታ አጋላጭ ያደርጋል።የሚመከረው የአልኮል መጠን – በቀን ለወንዶች ሁለት ቢራ እንዲሁም ለሴቶች አንድ ቢራ ብቻ ይመከራል።

  • ከመጠን በላይ ውፍረት(Obesity)፦ ይህ የውፍረት መጠን ለካንሰር በሽታ ያጋልጣል።
  • በአኗኗር ምክንያት የተገደበ እንቅስቃሴ ያላቸው ግለሰቦች፦ በቀን መደረግ ያለበትን የሰውነት የእንቅስቃሴ መጠን አለመከወን በራሱ ለአንጀት ካንሰር በሽታ ያጋልጣል። ምንም እንኳን የሰውነት የውፍረት መጠን ጥሩ ቢሆንም እንቅስቃሴ አለማድረግ በራሱ የሚፈጥረው ጫና ለዚህ በሽታ ያጋልጣል።
  • ሁለተኛው አይነት የስኳር በሽታ፦ ይህ በሽታ ያለባቸው ግለሰቦች በትልቁ አንጀት ካንሰር የመያዝ ዕድላቸው ሰፊ ነው።
  • ሲጋራ ማጨስ፦ ሲጋራ ማጨስ በትልቁ አንጀት ክፍል ውስጥ ዕጢዎች እንዲፈጠሩ ያደርጋል። እነኚህም ዕጢዎች(Polyps) በጊዜ ሂደት ወደ አንጀት ካንሰር የመቀየር ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።
  • በትልቁ አንጀት ውስጥ የበቀሉ ዕጢዎች መኖር፦ ይህ የሚኖር ከሆነ እና በምርመራ ከተረጋገጠ፤ ታካሚው በትንሽ ወራት ልዩነቶች የሚደረግ አጠቃላይ ምርመራ በየጊዜው ማድረግ ይኖርበታል ።
  • ከዚህ በፊት በአንጀት ካንሰር የተጠቃ ግለሰብ ከሆነ ወይም በሌሎች ካንሰር የተጠቃ ሰው በዚህ ካንሰር የመያዝ ዕድሉ ከፍተኛ ነው። ለምሳሌ፦ የደም ካንሰር(Lymphoma)፣ የወንድ ልጅ የዘር ፍሬ ካንሰር(Testicular Cancer) እንዲሁም የላይኛው የማህፀን ግድግዳ ካንሰር(Endometrial Cancer)
  • የትልቁ አንጀት መቁሰል ወይም የአንጀት ግድግዳ ምች(Croh’s Disease and Ulcerative Colitis)፦ የአንጀት ቁስለት በሽታ በረዥም ጊዜያት ሂደት ውስጥ ወደ ካንሰር የመለወጥ ዕድሉ ከፍተኛ ነው።
  • በቤተሰብ የሚወረሱ የዘረመል ለውጦች፡- በተለይ የትልቅ አንጀት ካንሰሩ ከ40 ዓመት በታች ባሉ ወጣቶች ላይ የሚከሰት ከሆነ፤  በዘረመል ለውጦች ምክንያትነት የመከሰት ዕድሉ ከፍተኛ ነው።

 ????የአንጀት ካንሰር እንዳይከሰት የሚረዱ ጠቃሚ ነገሮች ምንድን ናቸው?

????በተለይም ፍራፍሬዎችን፣ አረንጓዴ ቅጠላቅጠሎችን እንዲሁም ጥራጥሬን አዘወትሮ መመገብ በትልቁ አንጀት ካንሰር የመያዝ ዕድልን ይቀንሳሉ።

????የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ ፦ በሳምንት ከሶስት እስከ አምስት ቀናቶች ቢያንስ ለ30 ደቂቃዎች እንቅስቃሴን ማድረግ ከዚህ በሽታ ይታደጋል።

????አዘወትሮ የአንጀት ቁስለት መከላከያ መድኃኒቶችን መውሰድ(Like Aspirin and other micronutrients)  በበሽታው የመያዝ ዕድልን ይቀንሳሉ።

YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA

TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia

Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc

Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv

#NBC_ETHIOPIA

#ሆኖ_መገኘት

ShareTweetShare
Previous Post

አርቲስት መቅደስ ጸጋዬን የኢትዮጵያ ጨቅላ ህጻናት የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ሆነች

Next Post

ዝምተኛው ሐይቅ-ስልጤ አበያ!

Related Posts

⁨አዲስ ጥናት! _የማህበረሰብ ልማት ባለሞያ ዘላለም ይትባረክ! _NBC ቅዳሜ
Health

⁨አዲስ ጥናት! _የማህበረሰብ ልማት ባለሞያ ዘላለም ይትባረክ! _NBC ቅዳሜ

June 15, 2026
38
በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ መሠረተ ልማቶች ኢትዮጵያን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ትልቅ አቅም እየሆኑ ነው
Health

በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ መሠረተ ልማቶች ኢትዮጵያን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ትልቅ አቅም እየሆኑ ነው

June 4, 2026
24
⁨ሞት መድሃኒት አለዉ | ቆንጆ አለመሆኗ ሂዎቷን አመሰቃቅሎታል | ለራሳቸው መሆን የከበዳቸዉ ብዙ የህክምና ባለሙያውች አሉ | NBC ቅዳሜ
Health

⁨ሞት መድሃኒት አለዉ | ቆንጆ አለመሆኗ ሂዎቷን አመሰቃቅሎታል | ለራሳቸው መሆን የከበዳቸዉ ብዙ የህክምና ባለሙያውች አሉ | NBC ቅዳሜ

March 16, 2026
85
“ዳውን ሲንድረም የፈጣሪ ቁጣ ሳይሆን ስጦታ ነው!” | ውሎ በዲቦራ ፋውንዴሽን | በNBC እሁድ
Health

“ዳውን ሲንድረም የፈጣሪ ቁጣ ሳይሆን ስጦታ ነው!” | ውሎ በዲቦራ ፋውንዴሽን | በNBC እሁድ

February 17, 2026
48
ጥራቱ ያልጠበቀ ምርትን ለገበያ ሊያቀርቡ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ
Health

ጥራቱ ያልጠበቀ ምርትን ለገበያ ሊያቀርቡ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ

January 21, 2026
42
ወላጆች ስለ ልጆቻችችሁ ቶንሲል ግዴታ ማወቅ ያለባችሁ ነግሮች | ከታዋቂው የአንገት በላይ ስፔሻሊስት ሐኪም ጋር | NBC ጤና
Health

ወላጆች ስለ ልጆቻችችሁ ቶንሲል ግዴታ ማወቅ ያለባችሁ ነግሮች | ከታዋቂው የአንገት በላይ ስፔሻሊስት ሐኪም ጋር | NBC ጤና

August 25, 2025
89
Next Post
ዝምተኛው ሐይቅ-ስልጤ አበያ!

ዝምተኛው ሐይቅ-ስልጤ አበያ!

“በኢትዮጵያ ያለው የስራ ባህል የውጭ ተፅዕኖ ያረፈበት ነው”

"በኢትዮጵያ ያለው የስራ ባህል የውጭ ተፅዕኖ ያረፈበት ነው"

9000 የሚሆኑ የጎዳና ተዳዳሪዎች ከጎዳና ተነስተዋል ተባለ

9000 የሚሆኑ የጎዳና ተዳዳሪዎች ከጎዳና ተነስተዋል ተባለ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?