????የትልቁ አንጀት ካንሰር የሚባለው
አዲስ አበባ | ህዳር 10፤ 2016| NBC ETHIOPIA -መነሻውን ከትልቁ የአንጀት ክፍል ያደረገ ማንኛውም ካንሰር የትልቁ አንጀት ካንሰር በመባል ይታወቃል። ትልቁ አንጀት በርዝመት መጠኑም ሆነ በስፋቱ ትልቅ የሚባል ሲሆን ሰገራ እስከሚወጣበት የታችኛው የአንጀት ክፍል ድረስ ይዘረጋል።

በተለምዶ የምግብ መብላላት ዑደት ከላይኛው የምግብ ቱቦ (Esophagus) ጀምሮ በጨጓራ እና በትንሹ አንጀት በኩል ካለፈ በኋላ ትልቁ አንጀት ላይ ይደርሳል። ይህ የተብላላው የምግብ ክፍል የመጨረሻውን መዳረሻ ፊንጢጣ ላይ በማድረግ ከሰውነት ይወገዳል። የካንሰር በሽታ ከእነዚህ ክፍሎች መነሻውን የማድረግ ዕድሉ ከፍተኛ ነው።
????ለትልቁ አንጀት ካንሰር አጋላጭ ምክንያቶች ምንድናቸው?

-ዕድሜ ፦ በዕድሜ ጎልማሳ የሆኑ ግለሰቦች በዚህ በሽታ የመጠቃት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።
– አመጋገብ ፦ ለትልቁ አንጀት ካንሰር እንደዋነኛ አጋላጭ ምክንያትነት የሚታየው የተዛባ የአመጋገብ ስርአት ነው ። በተለይ ቀይ ስጋን አዘውትሮ መመገብ ለምሳሌ ፦ የበሬ፣ የአሳማ እንዲሁም የበግ ቀይ ስጋን አዘውትረው የሚመገቡ ግለሰቦች፤ የታሸጉ እና በፋብሪካ የተቀመሙ የስጋ ተረፈ ምርቶችን አዘወትሮ መጠቀም፤ የስብ መጠኑ ከፍ ያለን ስጋ አዘወትሮ መመገብ (ጮማ ስጋ)፤ የፋይበር መጠኑ ያነሰ ምግብን አብዝቶ መመገብ እንዲሁም አልኮልን ከመጠን በላይ አዘውትሮ መጠቀም ለዚህ በሽታ አጋላጭ ያደርጋል።የሚመከረው የአልኮል መጠን – በቀን ለወንዶች ሁለት ቢራ እንዲሁም ለሴቶች አንድ ቢራ ብቻ ይመከራል።
- ከመጠን በላይ ውፍረት(Obesity)፦ ይህ የውፍረት መጠን ለካንሰር በሽታ ያጋልጣል።
- በአኗኗር ምክንያት የተገደበ እንቅስቃሴ ያላቸው ግለሰቦች፦ በቀን መደረግ ያለበትን የሰውነት የእንቅስቃሴ መጠን አለመከወን በራሱ ለአንጀት ካንሰር በሽታ ያጋልጣል። ምንም እንኳን የሰውነት የውፍረት መጠን ጥሩ ቢሆንም እንቅስቃሴ አለማድረግ በራሱ የሚፈጥረው ጫና ለዚህ በሽታ ያጋልጣል።
- ሁለተኛው አይነት የስኳር በሽታ፦ ይህ በሽታ ያለባቸው ግለሰቦች በትልቁ አንጀት ካንሰር የመያዝ ዕድላቸው ሰፊ ነው።
- ሲጋራ ማጨስ፦ ሲጋራ ማጨስ በትልቁ አንጀት ክፍል ውስጥ ዕጢዎች እንዲፈጠሩ ያደርጋል። እነኚህም ዕጢዎች(Polyps) በጊዜ ሂደት ወደ አንጀት ካንሰር የመቀየር ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።
- በትልቁ አንጀት ውስጥ የበቀሉ ዕጢዎች መኖር፦ ይህ የሚኖር ከሆነ እና በምርመራ ከተረጋገጠ፤ ታካሚው በትንሽ ወራት ልዩነቶች የሚደረግ አጠቃላይ ምርመራ በየጊዜው ማድረግ ይኖርበታል ።
- ከዚህ በፊት በአንጀት ካንሰር የተጠቃ ግለሰብ ከሆነ ወይም በሌሎች ካንሰር የተጠቃ ሰው በዚህ ካንሰር የመያዝ ዕድሉ ከፍተኛ ነው። ለምሳሌ፦ የደም ካንሰር(Lymphoma)፣ የወንድ ልጅ የዘር ፍሬ ካንሰር(Testicular Cancer) እንዲሁም የላይኛው የማህፀን ግድግዳ ካንሰር(Endometrial Cancer)
- የትልቁ አንጀት መቁሰል ወይም የአንጀት ግድግዳ ምች(Croh’s Disease and Ulcerative Colitis)፦ የአንጀት ቁስለት በሽታ በረዥም ጊዜያት ሂደት ውስጥ ወደ ካንሰር የመለወጥ ዕድሉ ከፍተኛ ነው።
- በቤተሰብ የሚወረሱ የዘረመል ለውጦች፡- በተለይ የትልቅ አንጀት ካንሰሩ ከ40 ዓመት በታች ባሉ ወጣቶች ላይ የሚከሰት ከሆነ፤ በዘረመል ለውጦች ምክንያትነት የመከሰት ዕድሉ ከፍተኛ ነው።
????የአንጀት ካንሰር እንዳይከሰት የሚረዱ ጠቃሚ ነገሮች ምንድን ናቸው?

????በተለይም ፍራፍሬዎችን፣ አረንጓዴ ቅጠላቅጠሎችን እንዲሁም ጥራጥሬን አዘወትሮ መመገብ በትልቁ አንጀት ካንሰር የመያዝ ዕድልን ይቀንሳሉ።
????የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ ፦ በሳምንት ከሶስት እስከ አምስት ቀናቶች ቢያንስ ለ30 ደቂቃዎች እንቅስቃሴን ማድረግ ከዚህ በሽታ ይታደጋል።
????አዘወትሮ የአንጀት ቁስለት መከላከያ መድኃኒቶችን መውሰድ(Like Aspirin and other micronutrients) በበሽታው የመያዝ ዕድልን ይቀንሳሉ።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












