አዲስ አበባ | ህዳር 06 2016| NBC ETHIOPIA -በኢትዮጵያ ያለውን የትራንስፖርት ችግር በመመልከት ከዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ግሩኘ ያንጎ(YANGO) እና ከሀገር በቀሉ ብራንድ ሹፋሬ ጂ2ጂ (G2G) ግሩፕ ኩባንያ ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ የጉዞ አገልግሎትን በሂልተን ሆቴል በይፋ አስጀምሯል።

በኢትዮጵያ የያንጎ ስራ (YANGO) አስኪያጅ ዶ/ር ይከናለም አበበ በስምምነታቸው መደሰታቸውን ገልፀው “የያንጎን አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የራይድ አገልግሎት ከሹፋሬ ጋር ያደረግነውን ትብብር ለኢትዮጵያ ስናስተዋውቅ በጣም ደስተኞች ነን ያሉ ሲሆን በኢትዮዽያ ያለውን የትራንስፖርት ዘርፍ እንደሚቀይር በፅኑ እናምናለን ብለዋል።
የጂ2ጂ (G2G) አይቲ ግሩፕ ስራ አስኪያጅ አቶ ቴዎድሮስ መሃሪ በአጋርነታቸው ደስተኛ እንደሆኑ ገልፀው “ይህ ጅምር በኢትዮጵያ ለሚደረገው የራይድ-ሂይልንግ ኢንደስትሪ ጉልህ እድገትን ያሳያል ብለዋል። አክለውም ከያንጎ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎች አስተማማኝ እና ደንበኛን ያማከለ አገልግሎት ለማቅረብ ቆርጠው መነሳታቸውን ገልፀዋል።

የያንጎ መተግበርያ የሚጠቀሙ ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ውጭ ባሉ የአለም ሀገራትም በተመሳሳይ መተግበርያ በተመሳሳይ ዋጋ መጠቀም ይችላሉ::
የያንጎ የተሳካ የማሽከርከር አገልግሎት በአውሮፓ፣ በመካከለኛው እስያ፣ በደቡብ አሜሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በአፍሪካ በሚገኙ የአፍሪካ ሀገሮች የአይቮሪ ኮስት፣ ጋና፣ ካሜሮን፣ሴኔጋል፣ ዛምቢያ፣ አንጎላ፣ ኮንጎ ብራዛቪል፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ሞዛምቢክ፣ አልጄሪያ ጨምሮ ወደ አስራ ሶስት የአፍሪካ ሀገራት አሻራውን አሳርፋል፡፡
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












