አዲስ አበባ | ህዳር 03 2016| NBC ETHIOPIA – 18ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በሀገር አቀፍ ደረጃ በድምቀት እንደሚከበር የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር የበዓሉን አከባበር አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በዓሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በድምቀት እንደሚከበር ገልጸዋል፡፡
አፈ ጉባኤው 18ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል፤ በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነት እና በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት አስተናጋጅነት “ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በድምቀት ይከበራል ብለዋል፡፡
በዓሉ ከህዳር 25 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት እንደሚከበር የተገለጸ ሲሆን፤ ህዳር 25 የወንድማማችነት ቀን፣ ህዳር 26 የአብሮነት ቀን፣ ህዳር 27 የብዝኀነት ቀን፣ ህዳር 28 የመደመር ቀን፣ ህዳር 29 ደግሞ የኢትዮጵያ ቀን የሚል ስያሜ እንደተሰጣቸው የፌዴሬሽን ምክር ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram –https://t.me/nbcethiopiatv












