አዲስ አበባ | ህዳር 01 2016| NBC ETHIOPIA -የስኳር ህመም ያለበት ሰው ማድረግ ያለበት ህክምና እና መወሰድ ያለባቸው ጥንቃቄዎች እንደሚከተለው አስቀምጠናል:-

????ጤናማ አመጋገብ

– በየእለቱ በተመሳሳይና መደበኛ በሆነ ሰዓት መመገብ፣ አትክልት ቅጠላቅጠልና ፍራፍሬዎችን ማዘውተር፣ ጣፋጭ፣ ቅባትና ስብ የበዛበት ምግብ መቀነስ፣ በተለይም ደግሞ ከስኳር ህመም ውጭ ሌላ ተጓዳኝ ችግር ካለብዎ ለምሳሌ:- ደም ግፊት፣ የልብ ህመም፣ የሪህ በሽታና የጉበት ችግር ካለብዎ አመጋገብ ላይ ጥንቃቄ ለማድረግ ሐኪምዎን ማማከር ይጠበቅቦታል።
????????♂️ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

– በየዕለቱ ቢያንስ ለ 30 ደቂቃ ፈጠን ያለ እርምጃ የእግር ጉዞ ማድረግ
???????? ለእግር ተገቢዉን ጥንቃቄና እንክብካቤ ማድረግ

– በየዕለቱ የእግርን ዙሪያ ገባውን ማየት፣ የማይታየን የእግር ክፍል ካለ መስታወት መጠቀም፣
– ፈፅሞ በባዶ እግር አለመሄድ፣
-ከታጠቡ በኋላ የጣቶችን መሃል ጨምሮ እግርን በፎጣ ማድረቅ፣
– የእግር ጉዳት ወይም ችግር ካጋጠምው ወዲያውኑ ወደ ህክምና መሄድ፣
– ሲጋራ ፈፅሞ አለማጨስ
– የሰውነት ክብደትዎ ያለ ማቋረጥ የሚቀንስ ወይም በጣም የሚጨምር ከሆነ ሐኪምዎን ማናገር
???????? የአፍንና የጥርስን ጤንነት መጠበቅ

– ከምግብ በኋላ አፍን መጉመጥመጥ፣
– ጥርስን ቢያንስ በቀን ሁለት ጊዜ ማፅዳት
– በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን በየግዜው መከታተል፣
– አማካኝ የሶስት ወራት የስኳር ዉጤት ምርመራ ማድረግ
– ቢያንስ በአመት አንድ ጊዜ:- የአይን፣ የኩላሊት፣ የነርቭ፣ የልብ፣ የደም ቅባት (ኮሌስትሮል) ምርመራ እንዳስፈላጊነቱ ሐኪምዎት በሚያዘው መሰረት ማድረግ
???? የስኳር ህመም እንክብሎችን መውሰድ

– ሁለተኛው አይነት የስኳር ህመም ታካሚ ከሆኑ በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ለመቆጣጠር በሐኪም የታዘዘልዎትን እንክብል (መድሃኒት) ይዉሰድ።
???? ኢንሱሊን በተገቢው ሰዓትና ሁኔታ መውሰድ

– በዋናነት አንደኛው የስኳር ህመም አይነት ካለብዎ ሐኪምዎ ኢንሱሊን ሊያዝልዎት ግድ ይላል። ምክንያቱም በዚህኛው የስኳር ህመም አይነት ቆሽት ምንም አይነት ኢንሱሊን ስለማያመነጭ የሰውነታችን ህዋሳት በር ተከፍቶ ስኳር (Glucose) እንዲቀበሉና ከዚያም ስኳርን አቃጥለው ሃይል (ጉልበት) እንዲፈጠር የሚያደርግ ንጥረ- ቅመም (ኢንሱሊን) ግዴታ ከውጭ በመርፌ መውሰድ ያስፈልጋል። ይህም ሲሆን ደማችን ውስጥ ያለው የስኳር መጠን እንዲቀንስ፣ እንዲስተካከልና ህዋሳቶቻችን በቂ ስኳር እንዲያገኙ ያደርጋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












