አዲስ አበባ | ጥቅምት 30 2016| NBC ETHIOPIA -ኢትዮ ቴሌኮም “ዘላቂ የጋራ ማህበራዊ ሀላፊነት ለወገን ብሩህ ተስፋ” በሚል መሪ ቃል ከተመረጡ የበጎ አድራጎት ተቋማት ጋር ለዜጎች ለሚያደርጉት የሰብዓዊ እርዳታ የሚያግዝ የድጋፍ ስምምነት አካሄደ።

ተቋሙ ከተቋቋመበት የቢዝነስ ዓላማ በተጨማሪ ማህበራዊ ፋይዳ ባላቸው ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ የበኩሉን መልካም አሻራ እያሳረፈ እንደሚገኝ የገለፀ ሲሆን ይህን አስመልክቶ እገዛዎችን ለማከናወን የሚያስችል የድጋፍ ስምምነት ከተመረጡ ስምንት የበጎ አድራጎት ተቋማት ጋር አካሄዷል።
እነዚህም የበጎ አድራጎት ተቋሟት ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ፤ ጌርጌሲኖን የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማሕበር፣ የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ማዕከል፤ ኢትዮጵያ ካንሰር አሶሴሽን፣ ኸይር በጎ አድራጎት ድርጅት፣ መቄዶኒያ የአረጋዊያን መርጃ ማዕከል፣ ሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር እና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ሲሆኑ ድጋፎችን ከህዝቡ ለመቀበል እንዲያግዛቸዉ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮችን እና አጫጭር የፅሁፍ መልዕክት አማራጮችን ተቋሙ አስቀምጦላቸዋል ።
ኢትዩ ቴሌኮም በማህበራዊ እና ሰብዓዊ ሥራቸው ውጤታማ የሆኑ የበጎ አድራጎት ተቋማትን በጥናት በመለየት ወደ ኅብረተሰቡ ለመድረስ የሚያስችሉ የተለያዩ አሰራሮችን በመንደፍ እና ከተቋማቱ ጋር ያለውን አጋርነት ለማጠናከር የተለያዩ እቅዶችን ቀርጾ በመስራት ላይ እንደሚገኝም በውይይቱ ተገልጿል።
በአስናቀች መላኩ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv