አዲስ አበባ | ጥቅምት 30 2016| NBC ETHIOPIA – በማራካሽ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘዉ ፎረም በአፍሪካ ከተሞች አጠቃላይ ዕድሎች እና ተግዳሮቶች፤ እንዲሁም ለፈጣን የከተሞች ዕድገት የፋይናንስ ምንጭ በተመለከተ ውይይት መደረጉን በፎረሙ እየተሳተፉ የሚገኙት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባዋ የአዲስ አበባን የልማት ፍኖት፣ የፋይናንስ ስርዓታችንን እና የገቢ አሰባሰብ ልምድ ማጋራታቸውን ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።

በመርሐ-ግብሩ የተሳተፉ አለም አቀፍ እና አህጉራዊ ተቋማት ከተማችን አዲስ አበባ በፈጣን ለውጥ ውስጥ የምትገኝ ፣ የተረጋጋችና ሰላማዊ መሆኗን ጠቅሰው በአዲስ አበባ ከተማ ኢንቨስት ማድረግ አዋጭ እንደሆነ መግለፃቸውንም ከንቲባዋ አመላከተዋል፡፡
ሁሉንም የልማት ዕድሎች እና አቅሞችን በማስተባበር አዲስ አበባን ተወዳዳሪና ተመራጭ ከተማ የማድረግ ራዕያችንን እናሳካለን ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












