አዲስ አበባ | ጥቅምት 29፤ 2016| NBC ETHIOPIA -የመተንፈሻ አካላት በሽታ ሲሆን የተለያዩ ቫይረሶች ይሄን በሽታ ያስከትለዋል፡፡
ራስ ምታት

የጉንፋን (flu) የመጀመሪያ ምልክት የሚሆነው ከባድ ራስ ምታት ነው። አንዳንድ ጊዜ ብርሃን እና ድምፅ ራስ ምታትውን ያባብሱብናል፡፡
ትኩሳት

ጉንፋን ሁልጊዜ የሰውነት ሙቀት መጨመር ያስከትላል፡፡ ይህ ደግሞ ሰውነት ላይ ትኩሳት ይፈጥራል፡፡
ከጉንፋን ጋር የተያያዙ አብዛኛዎቹ ትኩሳቶች በ100°F (37.8°C) አካባቢ ካለ ዝቅተኛው ደግሞ ትኩሳት እስከ 104°F (40°C) ይደርሳል።
ከፍ ያለ የሙቀት መጠን ሲኖር ትኩሳት ሊሰማን ይችላል የሰውነታችን ከፍተኛ ሙቀት ቢኖርም ምልክቶቹ ብርድ ብርድ ማለትን፣ ላብን ያካትታሉ። አብዛኛዎቹ ትኩሳቶች ከ 1 ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ወይም ከ 3 እስከ 4 ቀናት አካባቢ ሊቆየ ይችላሉ፡፡
ሳል

ደረቅ፤የማያቋርጥ ሳል ከጉንፋን (flu) ጋር የተለመደ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ አንዳንድ ጊዜ የትንፋሽ ማጠር ወይም የደረት ላይ ምቾት መንሳት ሊሰማን ይችላል፡፡ ብዙ ከጉንፋን ጋር የተያያዘ ሳል ለ2 ሳምንታት ያህል ሊቆይ ይችላል፡፡
የጡንቻ ሕመም

ከጉንፋን ጋር የተያያዙ የጡንቻ ህመሞች በአንገት፣በጀርባ፣በእጅ እና በእግር ላይ በብዛት ያጋጥማሉ። ብዙውን ጊዜ ከባድ ስለሚሆኑ መሰረታዊ ስራዎችን ለመስራት በሚሞክሩበት ጊዜ እንኳን ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡
ድካም

የድካም ስሜት በጣም ግልጽ ያልሆነ የጉንፋን ምልክት ነው።
ምልክቶቹ ከባድ ከሆኑ፣ ከህመም በስተጀርባ ያለውን ለማወቅ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram -https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












