አዲስ አበባ | ጥቅምት 28፤ 2016| NBC ETHIOPIA -በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ መስፋፋትን ተከትሎ የሳይበር ጥቃት እየጨመረ ቢመጣም በአንፃሩ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው ንቃተ ህሊና አናሳ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ ተናግረዋል::

4ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር “አይበገሬ የሳይበር አቅም ለሀገር ሉአላዊነት” በሚል መሪ ሃሳብ ከጥቅምት 01/2016 ጀምሮ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ሲካሄድ ቆይቷል::

የሳይበር ደህንነት ወር የመጨረሻ መርሃ ግብር የሆነው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ምርምር ኮንፍረንስ እየተካሄደ ይገኛል::
በመድረኩም ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ በሳይበር ደህንነት ዝቅተኛ ደረጃ ላይ መቀመጧም ተነስቷል::
በአክረም ኑርያ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram –https://t.me/nbcethiopiatv












