አዲስ አበባ | ጥቅምት 20አዲስ አበባ | ጥቅምት 20 2016| NBC ETHIOPIA -የደቡብ ኮሪያዋ ቾንቹን ከተማ ከንቲባ ዩክ ዶንግ ሃን የሁለቱ እህትማማች ከተሞች የ20ኛ ዓመት ክብረ በዓል ለማክበርና ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ከልዑካን ቡድናቸው ጋር አዲስ አበባ ገብተዋል:: 2016| NBC ETHIOPIA -የደቡብ ኮሪያዋ ቾንቹን ከተማ ከንቲባ ዩክ ዶንግ ሃን የሁለቱ እህትማማች ከተሞች የ20ኛ ዓመት ክብረ በዓል ለማክበርና ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ከልዑካን ቡድናቸው ጋር አዲስ አበባ ገብተዋል::

ከንቲባ ዩክ ዶንግ ሃን ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ አቀባበል አድርገውላቸዋል::
ከንቲባ ዩክ ዶንግ ሃን የሁለቱ እህትማማች ከተሞች የ20ኛ ዓመት ክብረ በዓል ከማክበር በተጨማሪ የሁለቱን ከተሞች ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ማሸጋገር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር የሚመክሩ ይሆናል::
የልዑካን ቡድኑ በአዲስ አበባ ቆይታው ለአብርሆት ቤተ-መፅሃፍት መፅሃፍት ማበርከትን ጨምሮ በከተማዋ ከለውጡ ወዲህ የተገነቡ ታላላቅ ፕሮጀክቶችንና ትምህርት ቤቶችን የሚጎበኝ ሲሆን የሁለቱን ከተሞች የባህል ል ውውጥ ፌስቲቫል እንዲሁም ከኮሪያ ዘማች አርበኞች ጋር ቆይታ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል::
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv