አዲስ አበባ | ጥቅምት 21 2016| NBC ETHIOPIA -በአለም አቀፍ ደረጃ ለ44ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ36ኛ ጊዜ የሚከበረው የቱሪዝም ሳምንት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል::

ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣይ ሶስት ቀናት በመስቀል አደባባይ በሚቆየው የቱሪዝም ሳምንት “ቱሪዝም ለአረንጏዴ ልማት አረንጏዴ ልማት ለቱሪዝም ” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ይገኛል::

በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ል ከንቲባ ዣንጥራር አባይ ዘርፉ ለበርካታ ሀገራት ከፍተኛ የገቢ ምንጭነት እያገለገለ እንደሚገኝ አስታውቀዋል::
አክረም ኑርያ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv