አዲስ አበባ | ጥቅምት 14፤ 2016|- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ በኢትዮጵያ ፣ግብጽና ሱዳን መካከል በግብጽ ካይሮ ሲካሄድ የቆየው 3ኛው ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሀ ሙሌት እና አለቃቀቅ ደንቦች እና መመሪያዎች የሶስትዮሽ ድርድር መጠናቀቁን አስታውቋል።

ለሁለት ቀናት በተካሄደው መድረክ የሶስቱ ሃገራት ተወካዮች ጠንካራ ድርድር ማድረጋቸውንም አክሎ ገልጿል።
በድርድሩ ላይ በኢትዮጵያ በኩል በሚኒስትር ማዕረግ ዋና ተደራዳሪ አምባሳደር ስለሺ በቀለ ፣ በግብጽ በኩል የውሀ ሃብትና መስኖ ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ሃኒ ሰዊላም እንዲሁም በሱዳን በኩል በተጠባባቂ የመስኖና ውሀ ሃብት ሚኒስትር ዳወልበይት አብደልራህማን የተመሩ አባላት ተሳትፈዋል።
ተደራዳሪዎች ወደጋራ መግባባት በሚያደርሱ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት የተወያዩ ሲሆን በመጨረሻም ቀጣዩን ዙር ድርድር ለማካሄድ በፈረንጆቹ ታህሳስ 2023 አዲስ አበባ ላይ ለመገናኘት ተስማምተዋል።
ኢትዮጵያ በአባይ ውሀ አጠቃቀም ላይ ሁሉንም ወገን አሸናፊ የሚያደርግ ስምምነት ላይ ለመድረስ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግልጫው አስታውቋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv












