አዲስ አበባ | ጥቅምት 14፤ 2016| በዕጽዋት ዘረመል ማዳቀል እና ዓለም አቀፍ ግብርና ተመራማሪ፣ የፑርዱ ግሎባል የምግብ ዋስትና ማዕከል ዋና ዳይሬክተር፣ የፑርዱ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ዋስትና ፕሬዚደንት ባልደረባ የሆኑት ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጄታ የአሜሪካ ብሔራዊ የሳይንስ ሜዳሊያን ከፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እጅ ተረክበዋል።

ይህ ሽልማት አሜሪካ በተለያዩ ዘርፎች ለተሰማሩ ተመራማሪዎች የምትሰጠው ከፍተኛ እውቅና ነው።
ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጄታ በማሽላ እህል ላይ ሰፊ ጥናት ያደረጉ ሲሆን እ.አ.አ በ2009 የከፋ ድርቅ እና አጥፊ አረምን የሚቋቋሙ የማሽላ ዝርያን ላይ ባደረጉት ምርምር የዓለም ምግብ ሽልማትን ተቀዳጅተዋል ። ይህ ምርምራቸው ከፍተኛ የማሽላ ምርትን በመጨመር ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለመመገብ ረድቷል።
እንደ ኋይት ሀውስ ገለጻ ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጄታ ሽልማቱን ያገኙት በዕፅዋት ዘረመል ሳይንስ ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅኦ ነው። ድርቅን እና አረምን የሚቋቋም የማሽላ ዝርያን በማልማት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የምግብ ዋስትናን አሻሽሏል። የምርምር ውጤቶቹ ለሳይንስ፣ ለፖሊሲ እና ለተቋማት የኢኮኖሚ ልማት አስተዋጾ ከማበርከቱም በላይ የገበሬዎችን ህይወት በማሻሻል የሀገራትን ኢኮኖሚ ማጠናከር የቻለ ነው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv












