አዲስ አበባ | ጥቅምት 12 2016| NBC ETHIOPIA – ሶስተኛው ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት እና አለቃቀቅ ደንቦች እና መመሪያዎች የሶስትዮሽ ድርድር ዛሬ በካይሮ ተጀምሯል።

የኢትዮጵያ ወገን ተደራዳሪዎች ልኡካን መሪ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) በድርድሩ ላይ ባልተፈቱ የቴክኒካል እና የህግ ማእቀፍ ጉዳዮች የተሻለ ውጤት ላይ ለመድረስ ትኩረት እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡
አክለውም ኢትዮጵያ በ2015 በመሪዎች ደረጃ የተፈረመው የመርሆች መግለጫ ስምምነት መሰረት ድርድሩን በፍትሃዊና ምክንያታዊ አጠቃቀም መርህ መሰረት ውጤት ላይ ለመድረስ እንደምትሰራም ገልጸዋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












