አዲስ አበባ | መስከረም 29 2016| NBC ETHIOPIA- የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም ልምዳችንን በሀገር አቀፍ ልምድ ልውውጥ መድረክ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አረጋ ከበደ ፣ የሲዳማ ብሔራዊ ክልልዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ ፣ ሚኒስትሮች ፣ የኦሮሚያና የድሬዳዋ ከተማ አመራሮች ፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች እንዲሁም የመስኩ ባለሙያዎች በተገኙበት ልምዳቸውን ለክልሎችና ለከተማ አስተዳደሮች አካፍለዋል።

በተጨማሪም ከንቲባዋ ባለፉት 2 ዓመታት ለትውልድ ግንባታ ትኩረት በመስጠት ፣ የአስፈጻሚ ተቋማትን ቅንጅት በመፍጠር ፣ ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀትና በአሰራርና በአደረጃጀት ስራውን መምራታቸውን ተናግረዋል።
በዚህም ወላጆችንና አሳዳጊዎች በዕውቀት ሕጻናት እንዲያሳድጉ 2500 የቤት ለቤት ተንከባካቢዎችን አሰልጥነን አሰማርተን ፣ 56 ጤና ጣቢያዎችንና 46 ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችን አሸጋግረን ፣ 152 መዋለ ህጻናትን እና 156 የመጫወቻ ስፍራዎችን በመገንባት አዲስ አበባ ከተማን የሕጻናት ማደጊያ ምርጥ አፍሪካዊ መዲና ለማድረግ በትጋት በመስራት ያካበቱትን ልምድ ማጋራታቸውን ገልጸዋል።
አክለውም ለአፍሪካ ከተሞች ከንቲባዎች ልምዳችንን ያካፈልን ሲሆን ፤ የትውልድ ግንባታ ስራችን ( የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም) የሀገር አቀፍ ትኩረት እንዲሆን በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) ተወስኗል ብለዋል ።
በመጨረሻም ከንቲባዋ በስራዎቻችን ሁሉ ያልተቆጠበ ድጋፍ ያደረጉልንን ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በራሴና በከተማ አስተዳደራችን ስም ማመስገን እወዳለሁ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












