አዲስ አበባ | መስከረም 23 2016| NBC ETHIOPIA- ጃማይካ ውስጥ ሃሺሽ (ካናቢስ) ያለበት ከረሜላ የበሉ ከ60 በላይ ልጆች ሆስፒታል መግባታቸውን የሀገሪቱ የትምህርት ሚኒስትር ገልጿል።

ሚኒስትሯ ፋይፋል ዊሊያምስ በኤክስ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ (ትዊተር) ላይ እንደገለፁት፣ ልጆቹ ከጃማይካ ዋና ከተማ ኪንግስተን 80 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኝ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ መሆናቸው አስታውቋል።
ሚኒስትሯ እንዳሉት ልጆቹ ከረሜላውን ከበሉ በኋላ ማስታወክ እና መቃዠት አጋጥሟቸው ነበር። ነገር ግን ከተማሪዎቹ መካከል አንዳቸውም ከባድ የጤና ችግር አልተከሰተባቸውም። ሚኒስትሯ የከረሜላዎቹን ማሸጊያ ፎቶ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ያጋሩ ሲሆን፣ ከረሜላዎቹ ለሕጻናት የማይሰጡ መሆናቸው ተጽፎበታል።

ከረሜላው የተመረተው ሃሽሽ (ካናቢስ) በሕግ የተፈቀደ በሆነባት የአሜሪካ ግዛት ካሊፎርኒያ ውስጥ ሲሆን፣ በአሜሪካ የመድኃኒት አስተዳደር ፈቃድ ያገኘ ነው።
ከስምንት ዓመት በፊት ጃማይካ ማሪዋና ተብሎ የሚታወቀውን የካናቢስ እጽ በተወሰነ መጠን ይዞ መገኘትን በሕግ ፈቅዳለች።
ነገር ግን የአገሪቱ የጤና ሚኒስትር ክሪስቶፈር ቱፍተን እንደተናገሩት የጃማይካ መንግሥት እንደከረሜላ የተዘጋጀው እጽ ወደ አገሩ እንዲገባ አልፈቀደም።
ይህ ሁኔታ ጃማይካ ውስጥ የተከሰተው ደቡብ አፍሪካ ውስጥ 90 የሚደርሱ ልጆች እጽ የተቀባ ኬክ ከጎዳና ላይ ቸርቻሪ ገዝተው በመብላታቸው መተመማቸው ከተነገረ ከሳምንት በኋላ መሆኑን ቢቢሲ ዝግቧል።
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












