አዲስ አበባ | መስከረም 21 2016| NBC ETHIOPIA-በካሮሊንስካ ኢንስቲትዩት የሚገኘው የኖቤል ጉባኤ ለካታሊን ካሪኮ እና ድሩ ዌይስማን በኮቪድ-19 ላይ ውጤታማ የሆኑ የኤምአርኤን ክትባቶችን በመፍጠር የ2023 የኖቤል ሽልማት በፊዚዮሎጂ ወይም በህክምና ዘርፈ ለመሰጠተ ወሳኔ አሳለፏል ።

ሁለቱ የኖቤል ተሸላሚዎች እ.ኤ.አ. በ2020 መግቢያ ላይ በተከሰተው ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ውጤታማ የኤምአርኤንኤ ክትባቶችን ለማዘጋጀት ወሳኝ አካላት ነበሩ። እንደ ቢቢሲ ዘገባ በዘመናችን ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በሰው ልጅ ጤና ላይ ትልቅ ስጋት በነበረበት ወቅት ለክትባት እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረጋቸው ነው ሽልማቱ የተበረከተላቸው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












