አዲስ አበባ | መስከረም 21 2016| NBC ETHIOPIA-የጤና ሚኒስቴር ከባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 4ተኛው ሀገር አቀፍ የአፍላ ወጣቶች እና የወጣቶች ጤና ፎረም የመክፈቻ መርሀ ግብር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

ወጣቶች ችግሮቻቸውን በጋራ በመፈታት፣ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ፣ስለ ጤንነታቸው በቂ እውቀት እንዲኖራቸውና ሚዛናዊ ውሳኔዎች የመስጠት ልምድ እንዲያዳብሩ ፎረሙ መካሄድ ጉልህ ሚና እንዳለው በመርሀ ግብሩ ተነስቷል።
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የክልል የጤና ቢሮ ሀላፊዎች እና ከክልሎች የተወጣጡ ወጣቶች በፎረሙ ተገኝተዋል።
‹‹ጠንካራ አጋርነት ትርጉም ያለው የአፍላ ወጣቶችና ወጣቶች ተሳትፎ ለተሻለ ጤና>> በሚል መሪ ቃል ነው የጤና ፎረሙ እየተካሄደ የሚገኘው።
በሀሴት ሀይሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












