አዲስ አበባ | መስከረም 18 2016| NBC ETHIOPIA -ከሦስት ሚሊዬን በላይ ዜጎች ብሔራዊ መታወቂያ ለማግኘት የሚያስችላቸውን ምዝገባ ማድረጋቸውን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽህፈት ቤት ገለጸ።

የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽህፈት ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ራሔል አብርሃም እንደገለጹት በተያዘው የበጀት ዓመት 25 ሚሊዬን ዜጎች መታወቂያውን እንዲያገኙ እየተሰራ ነው።
አሁን ላይ ከሦስት ሚሊዬን በላይ ዜጎች የብሔራዊ መታወቂያ ለማግኘት ምዝገባ ማድረጋቸውን ገልጸው የምዝገባው ሥራ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በትብብር እየተከናወነ እንደሚገኝ አመልክተዋል።
በቀጣይ ሁኔታዎችን በማየት የዲጂታል መታወቂያና የቀበሌ መታወቂያ በተመጋጋቢነት ሊሰሩ የሚችሉበት ሁኔታ እንደሚፈጠርም ነው ያብራሩት።
በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት 90 ሚሊዬን ዜጎችን የብሔራዊ መታወቂያ ባለቤት ለማድረግ መታቃዱን ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
እቅዱ የተፈናቀሉ ዜጎች፣ ሰብአዊ እርዳታ የሚያሻቸውና ሌሎች ማንነታቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የማይችሉ ዜጎችን ታሳቢ ማድረጉ ተገልጿል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












