አዲስ አበባ | መስከረም 18 2016| NBC ETHIOPIA -ከዋና ከተማይቱ ካርቱም በስተምዕራብ በምትገኘው በኦምዱርማን ከተማ አል-ጃራፋ ሰፈር ውስጥ በሱዳን ልዩ ሀይል (RSF) በተፈጸመ ጥቃት10 ሰላማዊ ሰዎች መሞታቸውን የሱዳን ጦር አስታወቀ።

የሠራዊቱ ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄኔራል ናቢል አብዱላህ በሠራዊቱ ፌስቡክ ላይ በተለጠፈው የድምፅ ቅጂ ላይ “የአማፂው ሚሊሻ ጥቃቱን በመቀጠል በኦምዱርማን ከተማ የሚገኘውን አል-ጃራፋ ሰፈር ላይ ቦምብ በመወርወር ቤተሰብን ጨምሮ 10 ሰዎች ተገድለዋል” ብለዋል።
በሱዳን በጦር ኃይሉ እና በአርኤስኤፍ መካከል በተካሄደው ጦርነት 5,000 መሞታቸውን እና ከ5.2 ሚሊዮን በላይ መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ ያሳያል። በሳውዲ አረቢያ እና በአሜሪካ ሸምጋዮች የተደረደሩት በርካታ የተኩስ አቁም ስምምነቶች ሁከቱን ማስቆም አልቻሉም።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv
Facebook-https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












