አዲስ አበባ | መስከረም 12 2016| NBC ETHIOPIA – በኒው ዮርክ እየተደረገ ካለው 78ተኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ በተጓዳኝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከዩኒሴፍ ዋና ዳይሬክተር ካትሪን ሩሴልና ከኦቻ ኃላፊ ማርቲን ግሪፊትስ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ገለጻ አድርገውላቸዋል። ዩኔሴፍ በኢትዮጵያ ለሕጻናት በትምህርትና ጤና ዘርፎች እያደረገ ያለውንም ድጋፍ አድንቀዋል።የኦቻ ኃላፊ በኢትዮጵያ የተቋረጠውን የሰብዓዊ እርዳታ ማስቀጠል ያለውን ፋይዳ ለአቶ ደመቀ አንስተውላቸዋል።

የዩኒሴፍና ኦቻ ኃላፊዎች ሁለቱ ተቋማት ለሰላም ግንባታ ሂደቱ ከኢትዮጵያ ጋር የጀመሩትን ትብብር የመቀጠል ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በተመሳሳይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከዩኤንዲፒ ኃላፊ አቺም ስቴይነር ጋርም ተወያይተዋል።
በውይይታቸው ኃላፊው የተመድ የልማት ፕሮግራም ኢትዮጵያ የጀመረችውን የልማት ጉዞ በዘላቂነት እንድትቀጥል አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። የመልሶ ግንባታና ማቋቋም ለማገዝ ቁርጠኛ መሆናቸውን ኢ ፕ ድ በዘገባው አስታውቋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












