አዲስ አበባ | መስከረም 11 2016| NBC ETHIOPIA – በአሜሪካ በተለያዩ የኮንስትራክሽን ዘርፎች ላይ የካበተ ልምድ ያለው ኢስተርን ኮርፖሬሽን ኩባንያ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለሚሰሩ ሰራተኞች በተመጣጣኝ ዋጋ ቤቶችን ለመገንባትና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገለፀ።


በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የትራንስፎርሜሽን እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም ከተማ ከኩባኒያዉ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዴቪድ ሃምና ልዑካቸዉ ጋር ተወያይተዋል ።
በውይይቱ የትራንስፎርሜሽን እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ኃላፊው አቶ ፍፁም ከተማ ኢስተርን ኮርፖሬሽን በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢንቨስት ለማድረግና ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸዉን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለመገንባት ያሳየውን ከፍተኛ ፍላጎት አድንቀዋል።
የኢስተርን ኩባኒያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዴቪድ ሃም በበኩላቸው ኩባንያቸው በአሜሪካን ሃገር በተለያዩ ግንባታዎች ላይ ያካበተውን ልምድ በኢትዮጵያ ለማስፋፋት ማቀዱን ገልጸው በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክም ኢንቨስት በማድረግ በዘርፉ የራሱን አሻራ ለማሳረፍ ማቀዱን አሳውቀዋል፡፡
ኩባንያው በኮንስትራክሽን ዘርፍ ከ25 ዓመታት በላይ በቤቶች ግንባታ፤ እንዲሁም በፕሮጀክት ማስተዳደር ዘርፍ ልምድ ያለው ሲሆን ከ2000 በላይ ግንባታዎችን በማጠናቀቅ ለደንበኞቹ ያስረከበ ግዙፍ ኩባንያ መሆኑን ኢፕድ ዘገቧል፡፡
YouTube– https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok– https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook-https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA












