ዲስ አበባ | መስከረም10 2016| NBC ETHIOPIA -አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ትምህርት ዘመን በነባሩ ስርዓት የመደበኛ ተማሪዎችን እንደሚቀበል አስታውቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ÷ በዩኒቨርሲቲው እየተከናወኑ የሚገኙ የማሻሻያ ስራዎችን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ መሆኑን ተከትሎ የሽግግር ሒደት ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡የሽግግር ሂደቱ እስኪጠናቀቅ ድረስም ነባር አሰራሮች ባሉበት እንደሚቀጥሉ ነው የተናገሩት፡፡ ዩኒቨርሲቲው የሚቀይራቸው አሰራሮች ሲኖሩም በየጊዜው የማሳወቅ ስራ እንደሚከናወን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የራስ ገዝነት ሽግግር ጊዜ ከአንድ ዓመት እስከ አንድ ዓመት ተኩል እንደሚጠናቀቅም ተጠባባቂ ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram –https://t.me/nbcethiopiatv












