አዲስ አበባ | መስከረም 9 2016| NBC ETHIOPIA- በፀጥታ ችግር ምክንያት የተቋረጠውን ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ገቡ
በፀጥታ ችግር ምክንያት የተቋረጠውን ፈተና የሚወስዱ ከ11 ሺህ 581 በላይ ተማሪዎችን በተረጋጋ መልኩ ለማስፈተን ዝግጅት ማድረጉን ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ገለጸ፡፡

የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ ኀላፊ አቶ ዳንኤል ውበት 3 ሺህ 134 ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች መኖራቸውን ገልጸዋል። ለተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት ሲሰጥ መቆየቱን ተናግረዋል።
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ ኀላፊ አቶ ክንዱ ዘውዱ ተማሪዎች ዝግጅት እንዲያደርጉ ቀደም ብሎ መሠራቱን ገልጸዋል። በዞኑ 6 ሺህ 119 ተፈታኝ ተማሪዎች መኖራቸውን ኀላፊው አክለው አንስተዋል።
እንደ ኢፕድ ዘገባ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአሥተዳደር እና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ልጅዓለም ጋሻው ተማሪዎች በፀጥታ ችግር ምክንያት ፈተናቸውን ማጠናቀቅ አለመቻላቸውን በማስታወስ በአሁኑ ወቅት ፈተናውን ለመውሰድ ሙሉ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram –https://t.me/nbcethiopiatv