አዲስ አበባ | መስከረም 9 2016| NBC ETHIOPIA – በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እና በሸገር ከተማ አስተዳደር የኮዬ ፈጬ ከፍለ ከተማ የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት አከባበርን አስመልክቶ የጋራ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በሸገር ከተማ አስተዳደር የኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍቃዱ ቱሉ፤ በመስከረም ወር የሚከበረዉ የመስቀል እና የኢሬቻ በዓል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከርና በአላቶቹን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ባህላዊ ዕሴታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ የህብረተሰቡ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

የመስቀል በዓል ሀይማኖቱ በሚፈቅደዉ መልኩና ኢሬቻም የገዳ ስርአቱን በተከተለ ያለምንም የጸጥታ ችግር ማክበር እንደሚገባ ገልጸዋል።
ሁለቱም በአላት የአለም ቅርስ ሆነዉ በዩኔስኮ የተመዘገቡ በመሆናቸዉ በዓላቱ የመላዉ አለም መሆኑን በመገንዘብ እሴቱን ለማጥፋት የሚንቀሳቀሱ አካላት ማህበረሰቡ በጋራ መከላከል እንደሚገባ አሳስበዋል።
በምክክር መድረኩ የሁለቱ ክፍለ ከተሞች አመራሮችን ጨምሮ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተወጣጡ ነዋሪዎች ተሳታፊ መሆናቸውን ኢ ፕ ድ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram –https://t.me/nbcethiopiatv