በአዲስ አበባ | መስከረም 7 2016| NBC ETHIOPIA- ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ያላት ሀብት እንዳይባክንና ሌብነትን በቁርጠኝነት እንደሚታገሉ የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ገልፀዋል።

ለብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ”ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀው የመጀመሪያ ዙር ስልጠና በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው።
ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎም ይህንን የዕዳ ጫና በየደረጃው ቀንሶ ለሀገር ምንዳን ለማትረፍ ውስጣዊ ፀጋን፣ አቅምን የተፈጥሮ ሀብትን ጠንቅቆ ማወቅ የቅድሚያ ስራ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያን ለሁሉም ዜጎች የምትመች ሀገር አድርጎ በመገንባት በአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ ተግቶ መስራት፣ ሌብነትን በቁርጠኝነት በመታገል የሀብት ብክነት እንዳይኖር በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ነው የገለጹት።
የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ፤ ስልጠናው የብልፅግና ፓርቲ ለህዝቡ የገባውን ቃል ማስፈፀም የሚያስችል የአመራር አቅም የመፍጠር ዓላማን የሰነቀ መሆኑን በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ መግለፃቸው ይታወቃል።
ፓርቲው ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋጥ በሚያደርገው ጥረት በተለይም የአመራሩ የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነት ወሳኝ መሆኑን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram –https://t.me/nbcethiopiatv












