በአዲስ አበባ | መስከረም 7 2016| NBC ETHIOPIA- በስብሰባው ላይ ለመሳተፍ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች የተመድ ዋና መቀመጫ ወደ ሆነችው ኒው ዮርክ በመግባት ላይ ይገኛሉ።

ጠቅላላ ጉባኤው በአምባሳደሮችና በቋሚ መልዕክተኞች ደረጃ ነሐሴ 30/2015 መጀመሩ ይታወቃል።
“መተማመንን ዳግም መገንባት እና ዓለም አቀፍ አጋርነትን እንደገና ማደስ፤ የአጀንዳ 2023 እና የዘላቂ ልማት ግቦች ትግበራ በማፈጠን ለሁሉም ሰላም፣ ብልጽግና፣ ለውጥና ዘላቂነትን መፍጠር” የጉባኤው መሪ ቃል ነው።
በጉባኤው ሀገራት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተርን መሰረት በማድረግ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ይመክራሉ።
የ78ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዝዳንትና የትሪንዳድና ቶቤጎ ዲፕሎማት ዴኒስ ፍራንሲስ ጉባኤው ሰላም፣ ብልጽግና፣ ለውጥና ዘላቂነት ላይ ያተኮሩ መሆኑን ገልጸዋል።
ወረርሽኝን አስቀድሞ መከላከል፣ የልማት ፋይናንስ አቅርቦት፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች መከላከልና ምላሽ የጤና አገልግሎት ሽፋን ውይይት ከሚደረግባቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም በቅርቡ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ በ78ኛው የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ኢትዮጵያ የነቃ ተሳትፎ ለማድረግ ዝግጅት ማድረጓን መግለጻቸው ይታወቃል።
ጉባኤው በ174 አጀንዳዎች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል ያሉት አምባሳደር መለስ፤ ወደ ስፍራው የሚያቀናው የኢትዮጵያ ልዑክ በ55 አጀንዳዎች ላይ ንግግር በማድረግ የኢትዮጵያን አቋም ይፋ ያደርጋልም ብለዋል።
ኢትዮጵያ መድረኩን በመጠቀም አጋሮቿን በማብዛት ብሔራዊ ጥቅሞች እንዲረጋገጡና አህጉራዊ አጀንዳዎች እንዲሳኩ ለማድረግ በቂ ዝግጅት ማድረጓን ነው ቃል አቀባዩ የተናገሩት።
ኢትዮጵያ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከአገራት ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር እንደምትሰራም አብራርተዋል።
የ78ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ የከፍተኛ ስራ ኃላፊዎች ስብስባ እስከ መስከረም 15/2016 እንደሚቆይ ኢዜአ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












