አዲስ አበባ | መስከረም 7 2016| NBC ETHIOPIA – እንግሊዛዊው የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች ጋሪ ኔቭል፣ ማንችስተር ዩናይትድ ለደካማ የፕሪሚየር ሊግ ጅማሮ የተዳረገው በተጨዋቾች የቁርጠኝነት ማነስ አለመሆኑን ተናግሯል። ስብስቡ ከቁርጠኝነት ይልቅ ጥራት ያላቸው ተጨዋቾች እጥረት አለበት ብሏል።

የ48 አመቱ ጋሪ ኔቭል ዩናይትድ በክረምት የዝውውር መስኮት ያዘዋወራቸው ተጨዋቾች ያለበትን ክፍተት እንዳልሞሉለት ለስካይ ስፖርትስ ተናግሯል።
ክለቡ በዘንድሮው የክረምት የዝውውር መስኮት ለተጨዋቾች ዝውውር 183.5 ሚሊዮን ፓውንድ ሂሳብ አውጥቶ ያዘዋወራቸው ሰባት ተጨዋቾች የቡድኑን ደረጃ ከፍ አድርገዉታል የሚል ስሜት አይሰማኝም ብሏል።
ሃሪ ኬን ና ዴክላን ራይስን ማዘዋወር እንደነበረባቸው አክሏል።
የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ ቡድን በ2023-24 የውድድር አመት ካደረጋቸው ያለፉ አምስት የሊግ ጨዋታዎች ስድስት ነጥቦችን ብቻ በመሰብሰብ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 13ኛ ላይ ተቀምጧል።
በተለይም ባሳለፍነው ቅዳሜ በሜዳው በብራይተን የ3-1 ሽንፈት ካስተናገደ በኋላ ከእየአቅጣጫው ለሚጎርፉ ትችቶች ተዳርጓል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram –https://t.me/nbcethiopiatv












