
የአዲስ አበባ | መስከረም 5 2016| NBC ETHIOPIA-በምሥራቅ ሊቢያ የሚገኘው የቤንጋዚ አስተዳደር በሀገሪቱ በጎርፍ አደጋ ምክንያት ከሞቱት መካከል አብዛኞቹ ቤት እንዲቆዩ የተደረጉ በመሆናቸው ላደጋው ተጋላጭ እንዲሆኑ ተደርጓል ተብሎ የቀረበበትን ክስ አጣጥሏል።
የቤንጋዚ ቃል አቀባይ ኦስማን አብዱል ጃሊል እንዳሉት ነዋሪዎች የጎርፍ አደጋውከተከሰተበት ደርና አካባቢ እንዲሸሹ ነው የተነገራቸው ብለዋል። ከቤት እንዲቆዩ የተነገረ መልዕክት እንደሌለም ቃል አቀባዩ አክለው ተናግረዋል።
ሰዎች ለቀው እንዳይወጡ መነገራቸውን አስተባብለው፣ ነገር ግን አንዳንዶች ዛቻው የተጋነነ እንደሆነ ተሰምቷቸው ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል። በማዕከላዊ ደርና ሰዎችን ለማዳንና የሞቱ ሰዎችን ማንነት ለመለየት ርብርብ እየተደረገ ነው ተብሏል።
በደርና በደረሰው ጎርፍ ሳቢያ የሟቾች ቁጥር ከ6,000 እስከ11,000 ሲደርስ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ የደረሱበት አልታወቀም።
በሌላ በኩል የደርና ከንቲባ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ወደ 20,000 ሊደርስ እንደሚቸል ስጋታቸውን ገልፀዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebookhttps://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram -https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












