አዲስ አበባ | መስከረም 4 2016| NBC ETHIOPIA- በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በቡድን 77 እና የቻይና መሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የኩባ ዋና ከተማ ሃቫና ገብቷል፡፡

አቶ ደመቀ እና የልዑካን ቡድኑ ኩባ ሲደርሱም በሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሀላፊዎችና እና በኩባ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ጉባኤው በአሁኑ ወቅት የልማት ፈተናዎችን ለመወጣት የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና የኢኖቬሽን ሚና ላይ እንደሚመክር መጠቆሙን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል::
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv












