በዓባይ ግድብ ሃይል የሚያመነጩ ተርባይኖችን ቁጥር 7 ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ፡፡


በ2014 ዓ.ም ሃይል ማመንጨት ከጀመሩት ሁለት ተርባይኖች በተጨማሪ በያዝነው 2016 በጀት ዓመት 5 ተርባይኖችን ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ ነው፡፡
5ቱ ተርባይኖች ወደ ስራ ሲገቡ ኢትዮጵያ አሁን ላይ ያላትን 4 ሺህ 818 ሜጋ ዋት የሃይል አቅርቦት መጠን ከፍ ያደርገዋል ብለዋል ፡፡
ወደ ስራ ከገቡት ሁለት ተርባይኖች አንጻር ዘንድሮ ወደ ስራ የሚገቡት 5ቱ ተርባይኖች ሃይል መጠን የበለስ ፣የግልገል ጊቤ አንድና ሁለት እንዲሁም የተከዜ የሃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ከሚሰጧቸው አማካይ 1 ሺህ 180 ሜጋ ዋት ተመጣጣኝ ወይም የሚበልጥ ሃይልን ያመነጫሉ ብለዋል።
ይሁንና ከአቀማመጡና ከውሃ ፍሰቱ አኳያ የእነዚህን አምስቱ የሃይል ማመንጫ ተርባይኖች ሃይል የማመንጨት አቅም አሁን ላይ ይህን ያህል ነው ብሎ መናገር እንደማይቻል ገልጸዋል፡፡
ግድቡ ግንባታ ሲጠናቀቅ በ13ቱ ተርባይኖች 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይልን ወደ ብሄራዊ የሃይል ቋት እንደሚቀላቀልም ነው ሚኒስተሩ የገለጹት፡፡
በዚህም እያንዳንዳቸው ተርባይኖች በአማካይ ከ375 በላይ ሜጋ ዋት ሃይልን ያመነጫሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል ኢፕድ ዘግቧል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv