አዲስ አበባ | ጳጉሜ21 2015| NBC ETHIOPIA -ኢትዮጵያን በቀጣዮቹ 15 አመታት ዉስጥ የአቪዬሽን ማዕከል ወይም ሀብ ለማድረግ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ላለፉት ወራት ከፍተኛ ዝግጅት አድርጌበታለዉ ያለዉንና በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነዉን የአቪዬሽን ኢኖቬሽን ኤክስፖ ሊከፍት መሆኑን አሳዉቋል።

የዝግጅቱ ዋና አላማ በአቪዬሽን ፈጠራ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎችንና ልዩ ልዩ አካላትን ዕዉቅና በመስጠት በመደገፍና በመበረታታት የአቪዬሽን ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን እንዲስፋፋ ማድረግ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን የአቪዬሽን የፈጠራ ዉጤቶችን፣ ምርቶችና አገልግሎቶች ለኢንዱስትሪ ባለድርሻ አካላትና ለህብረተሰቡ ኤግዚቢት የሚደረጉበት የአቪዬሽን ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ መድረክ መፍጠር እንደሆነ ተጠቅሷል።
ይህ ኤክስፖ በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ባለቤትነት እንዲሁም በትራንስፖርት ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር አስተባባሪነትና ከሌሎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ እንደሆነ ተነስቷል።
ከጥቅምት 13-17 /2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም “የአቪየሺን ኢኖቬሽን ለላቀ ተወዳዳሪነት” በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄድም ተገልጿል።
ሊያ ክብሮም
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv