አዲስ አበባ | ጳጉሜ 1 2015| NBC ETHIOPIA-የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ለዘመን መለወጫ በዓል ከ5ሺህ በላይ የዕርድ እንሰሳት ማዘጋጀቱን ሲገልጽ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 211ሚልዮን ብር ትርፍ ማግኘቱንም አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አታክልቲ ገብረሚካኤል ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል ያለውን ዝግጅት አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንዳሰታወቁት ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል 5ሺህ የእርድ እንሰሳትን አዘጋጅቷል። ከዚህ ውስጥም ሁለት ሺህ በግና ፍየል መሆናቸው ኢ ፕ ድ ገልጿል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv
#ሆኖ_መገኘት












