አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26/2015፣ NBC ETHIOPIA-በ2016 የትምህርት ዘመን አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በሁሉም የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። አምስት የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይገነባሉ፡፡
የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሚኒስቴሩ በትምህርት ዘርፉ ላይ የተደረገውን ለውጥና የተከናወኑሥራዎችን አስመልክቶ ትናንት መግለጫ ሰጥተዋል።
በአጠቃላይ ሥርዓተ ትምህርቱ ላይ የነበረውን ስብራት ለመጠገን መሠረት የሚጥሉ የለውጥ ሥራዎች መከናወናቸውንም ፕሮፌሰር ብርሃኑ ገልጸዋል።በዚህም በ2015 ዓ.ም አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ተግባራዊ መደረጉን አመልክተዋል።
በ2016 የትምህርት ዘመን አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት በሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ጠቁመዋል። የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የሚያግዙ የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ ሲሆን፤ ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶች እንዲኖሩም በትኩረት ይሠራል ብለዋል።
በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች በኦንላይን እንደሚሰጥ ኢፕድ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebok-https://www.facebook.com/ethiopiannbc












