አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25/2015፣ NBC ETHIOPIA የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ከጅቡቲ ወደቦች ዓለም አቀፍ ነፃ የንግድ ቀጠና ሊቀመንበር ጋር ውይይት አድርገዋል።

በውይይታቸው የኢትዮ-ጂቡቲ ኮሪደር እንቅስቃሴና የወደብ ሥራ አገልገሎት አቅም ማሻሻል ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።
ለሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክተው የዶራሌ ሁለገብ ወደብ እና የጅቡቲ ካርጎ ተርሚናል አስተዳደራዊ የአሠራር ክፍተቶችን በመቅረፍ የዝውውር ፍሰትን ማቀላጠፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ከስምምነት ተደርሷል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook –https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












