በአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24/2015፣ NBC ETHIOPIA- ባሳለፍነው ቅዳሜ በጋቦን የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ ወታደራዊ አመራሮች ምርጫው ተጭበርብሯል በሚል ፕሬዝዳንት አሊ ቦንጎን ከሥልጣን አንስተው መንግስታዊ መንበሩን መቆጣጠራቸውን አስታውቀዋል ።

ወታደሮቹ በሀገሪቱ ቴሌቭዥን ጣቢያ ባስተላለፉት መልዕክት የጋቦንን አስተዳደር መያዛቸውን ተናግረዋል። በተጨማሪም በብሔራዊ ቴሌቭዥኑ የቀረቡት አስራሁለት ወታደሮች የምርጫውን ውጤት እንደሰረዙት ገልጸዋል።
ጋቦን ሀያ አራት በተባለው የቴሌቪዥን ጣቢያ በመቅረብ ፤ ይሄንን መጥፎ አስተዳደር በመገርሰስ ሰላምን ለማስፈን ውሳኔ ላይ ደርሰናል ሲሉም ተደምጠዋል።
በምርጫው ውጤት ፕሬዝዳንት አሊ ቦንጎ ሁለት ሦስተኛ ድምጽ አግኝተው እንዳሸነፉ የምርጫ ኮሚሽን ገልጾ እንደነበር አልጀዚራ ዘግቧል።
በቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












