በአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23/2015፣ NBC ETHIOPIA-አንድ የ20 ዓመት ወጣት ከ 41 ዓመት ሰው ጋር ህጋዊ ያልሆነ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጽሟል” በሚል በከባድ ግብረ የሰዶማዊነት ተከሷል፤ ይህም በግብረ ሰዶማዊነት የተከሰሰ የመጀመሪያው ኡጋንዳዊ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
በቅርቡ በኡጋንዳ በፀደቀው ህግ ፤ ግብረ ሶዶማዊነት በሞት የሚያስቀጣ ወንጀል መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡
ህጉ ከሀገሪቱ ውጭ ሰፊ ትችቶችን ያስከተለ ሲሆን የዓለም ባንክ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ለኡጋንዳ የሚሰጠውን ብድር እንዲያቆም አድርጓል። ኡጋንዳ ከ 2005 ጀምሮ የሞት ቅጣት ባትፈጽምም የሞት ቅጣት ግን በህጓ ውስጥ አልሰረዘችም።
በኡጋንዳ ህጉ ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ አራት ሰዎች በህጉ መሰረት ክስ እንደተመሰረተባቸው የዘገበው አልጀዚራ የዜና ወኪል ነው።
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












