አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23/2015፣ NBC ETHIOPIA – ስራ ና ክህሎት ሚኒስቴር በስዉዲን ለዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር የሚያደረገዉን ስራ ለማጠናከር ከስዊዲኑ ሚሊጆንብ ማይኒግ ተቋማ ጋር ስምምነት አካሂዷል

በስምምንቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት የስራ ና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ኢትዮጵያኖች ወደ ተለየያዩ አለማችን ሀገራት ተዛዉረዉ ስራ ለመስራት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በህጋዉ መንገድ የተመራ እንዲሆን ስራ ና ክህሎት ሚኒስቴር የተለያዩ ስልጠናዎችን ለዜጎቻችን በመስጠት ወደ ዉጭ እየላከ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ሚኒስትሯ ከስዊዲኑ ሚሊጆንብ ማይኒግ ተቋማ ጋር የተደረገዉ ስምምነትም በዉጭ አገራት ስራን ለመስራት ለሚሹ ወገኖች ስራን ከመፍጠር በተጨማሪ በቴክኖሎጂ የካበተ እዉቀት ያላቸዉ ዜጎችን ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና አለዉ ብለዋል፡፡
ስራ ና ክህሎት ሚኒስቴር በ2015 በጀት ዓመት 106 ሺ ዜጎች በህጋዊ መንገድ ወደ ዉጭ አገራት የስራ እድል እንዲያገኙ መደረጉም ተነስቷል፡፡
የስራ ና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ወደ ዉጭ አገራት የሚሄዱ ዜጎች የሰለጠኑ እንዲሆኑ የሚሰራዉን ስራ ለማገዝ ይህን መሰል ስምምነቶች ወሳኝነት አላቸዉ፡፡
ስምምነቶቹም ዜጎች ለስራ በሚሄዱበት አገር ተገቢዉን የስራቸዉን ክፍያ እንዲያገኙ እንዲሁም ደህንነታቸዉ የተጠበቀ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና አለዉ ብለዋል ፡፡
በሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/