በአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22/2015፣ NBC ETHIOPIA – ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ መድረክ በመወከል ቀዳሚ ከሆኑት መከካል አንዱ የሆነው ቦክሰኛ በቀለ አለሙ (ጋንች) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

የ3 ጊዜ የኦሎምፒክ ተሳታፊው በቀለ ዓለሙ በ82 ዓመቱ ነው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው።
ቦክሰኛ በቀለ በሮም፣ በቶክዮ እና በሜክሲኮ ኦሎምፒክ በቦክስ ዘረፍ ኢትዮጵያን ወክሎ ተሳትፏል።
ከሜሲኮው ኦሎምፒክ የተሳትፎ ሜዳሊያም ያገኘ ሲሆን የሌጎስ የአፍሪካ ሻምፒዮን መሆኑም የህይወት ታሪኩ ያስረዳል።

ቦክሰኛ በቀለ አለሙ የህይወት ታሪኩን የሚዳስስ “ያልተነገረለት የአገር ባለውለታ “በሚል ርዕስ በ2004 ዓ/ም መጽሐፍ ታትሞለታል።
በ1933 ታህሳስ 29 የተወለደው ቦክሰኛ በቀለ አለሙ፤ የ11 ልጆች አባት ነበር።
የቦክሰኛ በቀለ ዓለሙ የቀብር ስነ-ስርዓት በነገው እለት ቀትር 6 ሰዓት ላይ በሸጎሌ ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን እንደሚፈፀም የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












