አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22/2015፣ NBC ETHIOPIA- የገንዘብ ሚኒስቴርና የዓለም ባንክ ለአፍሪካ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ኮሪደር ፕሮጀክት (በኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር ፕሮጀክት) የ730 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያን 90 በመቶ የባህር ንግድን የሚይዘው ስትራቴጂካዊው ከአዲስ አበባ-ጅቡቲ ኮሪደር ጋር በተሳሰረ መልኩ የኢትዮጵያን የሎጅስቲክስና የትስስር አቅም እንደሚያጎለብት ተገልጿል።
በስምምነቱ መሰረት ለሜኦሶ-ድሬዳዋ መንገድ ግንባታ የፋይናንስ ድጋፍ የሚደረግ ሲሆን ግንባታው የትራንስፖርት አቅምና ብቃት የሚጨምር መሆኑንም የገንዘብ ሚኒስቴር ገልጿል።
መንገዱ በሚገነባባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎች የጤና፣ ውሃና ትምህርት አገልግሎት ተደራሽነት ጨምሮ ሌሎች መሰረተ ልማቶች ድጋፍ እንደሚደረግም አመልክቷል።
የገንዘብ ሚኒስትርና የወቅቱ የሆርን ኦፍ አፍሪካ ኢኒሺዬቲቭ ሊቀ-መንበር አቶ አህመድ ሺዴ ለዓለም ባንክ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ ትስስር መጎልበት በቁርጠኝነት ትሰራለች ማለታቸውን አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/